የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ የ2016 በጀት የ6 ወራት የአስፈጻሚ መ/ቤቶች አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው የዞኑ ሽግግር ምክር ቤት የቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሞ አስተያየት ሰጥተዋል።


በአስፈፃሚ መ/ቤቶች የሚስተዋሉ የመፈፀም ክፍተቶችን በመለየት የሚናገለግለው ህዝባችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ በኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦት ዙሪያ የሳይት ፕላን አሰጣጥ የፍትሃዊነት መጓደልና የህገ ወጥ ግንባታ መስፋፋትን ለመከላከል ትኩረት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ አሳስቧል።

በኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ዲያስፖራ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አውስተዋል።

በውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ በኩል ከማዕድን አስተዳደር ጋር ተያይዞ ክፍተት መኖሩ፣ በዘርፉ ለተደራጁ ማህበራት ትኩረት ባካለመሰጠቱ ህዝቡ ማግኘት ያለበትን ልማት ባለማግኘቱ የምክር ቤቱ አባላት በአስተያየታቸው አክለዋል።

በኮንሶ ዞን ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሂደት ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነፃፀር የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አፈፃፀም አናሳ በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ለሚደረገው ርብርብ ይጠናከር ብለው ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ትኩረት መስጠት ከትምህርት ዘርፉ እንደሚጠበቅ የምክርቤቱ አባላት አስገንዝበዋል።

የግብርና መምሪያ የበጋ ስንዴ እንዲሁም የፍራፍሬ ሰብሎች አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆኑን የተገነዘበው ምክር ቤት፤ ለአርሶ አደሩ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

በህብረት ስራ ልማት ፅ/ቤት በኩል የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ማስመለስ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ህገ ወጥ የቤንዚን ዝውውር እንቅስቃሴዎችን መበራከትና የፍጆታ ዕቃዎች አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የፍትሃዊነት መጓደል መኖሩም ምክር ቤቱ ገምግሟል።

ከካራት ሠገን እንዲሁም ከፓስቃ ወደ ፋሻ የሚወስደው መንገዶች ትኩረት ያልተሰጣቸው በመሆናቸው መስተዳድር ምክር ቤት ትኩረት እንዲሰጥ ህዝብ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

የፋይናንስ ሴክተርን የህዝብና የመንግስት ሀብት ቁጥጥሩን እንዲያጠናክሩና ብልሽቶቹን ኦዲት እንዲደርጉ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

በፀጥታ ጉዳይ ለተነሳው ጥያቄ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በእርሻ መሬት ዙሪያ የሚከሰቱ ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎችን በማምከን ከአጎራባች መዋቅሮች ጋር ያለው ሰላም ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

የተከበረው ምክር ቤት አባላት ላነሱት ጥያቄዎች አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ ለተሰነሱ በርካታ ጥያቄዎች የማጠቃለያ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በግብርና፣ በመንገድ፣ በማዕድን፣ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ በውሃ እና በፀጥታ ጉዳይ ሰፍ ማብራሪያ ሰጥተው፥ በፌስቡክ አሉባልታ የሚፈርስና የሚገነባ ሀገር የለምና እነኛ የጥፋት ሴራ አራማጆችን መንግስት ክትትል አድርጎ በህግ እስኪያስጠይቅ ተባብረን እንስራ ብለዋል።

የቀረበው የ2016 የግማሽ አመት የአስፈፃሚ መስሪያ ቤት ሪፖርት በአንድ ድምፀ ታቅቦና በአብላጫ ድምፅ በምክር ቤቱ ፀድቋል።

መረጃ
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዚያ 01/2016 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *