በጉባአኤው ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ለምክር ቤቱ ቀርቦ ይፀድቃሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጋቢት 30/2016 ዓ/ም እንደሚካሄድ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ አስታወቁ።
በምክር ቤቱ 8ኛ መደበኛ ጉባኤው አሠራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ማጽደቅ፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ መርምሮ እንደሚያጸድ እና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ፣ የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ እንዲሁም የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጨረሻ ንቅናቄ መድረክ በጉባኤው ለአባላቱ እንደሚቀርብ እና ዞናዊ ንቅናቄን በጋራ በማካሄድ ለውጤት ለመስራት ቃል ይገባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው ዕለት ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተባለው ትክክለኛ ሰዓት እንዲትገኙም ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መመምሪያ
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም
__________







