Ethio_Konso የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ በማስፋፊያ አከባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጊዜአዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና እየሰጠ ነው።


በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሻካይቶ ሳይሙሮ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ልዩነታችን ዉበታችን ነው ብለው ከማእከሎቻችን አንዷ ወደ ሆነችው ካራት ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

በሁሉም አከባቢ የራሳቸው ፀጋዎችና ትሩፋቶች ያሉ ሲሆን በአኛም አከባቢ በርካታ እሴቶች እና ባህላዊ ቅርሶች ስለሚገኙ በሚኖራችሁ ቆይታ እንዲተ‍እጎበኙ ስሉ የመንግስት ተጠሪው ጋብዘዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እና የመሬት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሄለን ዮሐንስ ከዚህ ስልጠና በኋላ ከተሞቻችን ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ ማበጀት ያስችላል ብለዋል።

ለከተሞቻችንን እድገት ማነቆ የሆነው የህገወጥ መሬት ወረራን በመከላከል እና በከተማ ዙርያ ላሉ አርሶ አደሮች ጊዜያዊ ሰርተፍኬት በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስቀረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የመሬት አሰተዳደር ዳይሬክተር ዶ/ር ጳውሎስ በርጉዳ የከተሞች ማስፋፊያ አከባቢ ጊዜአዊ የመሬት ሰርተፊኬት አሰጣጥ እና ህገወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ እያቀረቡ ነው።

ቀሪ መረጃዎች ከአፍታ ቆይታ በኋላ የመናደርስ ይሆናል

መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
መጋቢት 20/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *