በኮንሶ ዞን በዛሬው ዕለት የተከበረውን የሴቶች ቀን/ማርች 8ን አስመልክቶ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ ተካሄደ፣
በዞኑ ከሁሉም መዋቅሮች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በካራት ከተማ ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን/ማርች 8 በድምቀት የተከበረ ሲሆን፤ ዕለቱን ታሳቢ በማድረግ የዞኑ እና የካራት ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ አካሂደዋል።
ምርመራውን ካደረጉት መካከል በዞኑ ህዝብ ምክር ቤት የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ብዥቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ኩሲያ እና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ኮራ የሚገኙበት ሲሆን፤ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራን በማድረግ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ፤ ምናልባት የበሽታው ተጠቂ የመሆን አጋጣሚ ሲኖርም በጊዜ ተገቢውን ህክምና በማድረግ ራስን ማዳን ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
በመሆኑም ምርመራውን እንዳታደርግ የሚገድቧት ሳይንሳዊ ነገሮች የሌሉባት ማንኛዋም ሴት መመርመርና በቶሎ ራሷን ማወቅ ይገባታል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ምርመራውን ያደረጉት የዞኑ እና የካራት ከተማ አስተዳደር ሴት የመንግስት የስራ ኃላፊዎቹ።
መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት
መጋቢት 02/2018 ዓ.ም












