




“ሠላም ከፈጣሪ የተሰጠን የማይነጥፍ ሀብት ነው!” ሲሉ በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ አባቶች ተናገሩ።
የወረዳው ህዝብ ለሠላም የሚከፈል ዋጋ ሁሉ እንከፍላለንም ሲሉ ተደምጠዋል።
ለወረዳዉ ሠላም ዘብ በመቆም የሠገን ዙሪያ ወረዳን በልማት፣ በአንድነትና በብልፅግና ለማበልፀግ ሠላምና ፍቅር የመጨረሻ ምርጫችን ነው ብለዋል።
ከኮንሶ ዞን ማዕከል አባቶች በሠገን ዙሪያ ወረዳ አይሎታ፣ ደካቱ፣ መለጋና ዱካያ፣ ሠገን ገነት፣ ሉልቱ፣ ሰገን ከተማ፣ አዲስ ገበሬ፣ ብርብርሳ፣ ገርጨ እና የበቾ ቀበሌያት ከተውጣጡ ሽማጊሌዎች፣ ባህል አባቶችና የተለያዩ ማህበራዊ መሰረት ያላቸው አካላት ጋር ባህላዊ የሠላም ዕሴት ግንባታ ስርዓት አስፈፅመዋል።
አባቶች የፈፀሟቸው ባህላዊ ስርአቶች ለቀጠናው ሠላምና ልማት መልካም መሠረት እንዲሆን ተመኝተዋል።
የተጀመረውን ሠላም ለማስቀጠልና የወረዳዋን ሁለንተናዊ ሠላም ለማረጋገጥ የሠገን ከተማ አባቶች ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።







