የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኩሴ ጭሎ በተማሪዎች ሽኝት ወቅት እንደተናገሩት ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ለማድረስ በርካታ ተግባራት ተከናውነው ለሽኝት የበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በወሰዱት ኦሬንቴሽን እና ቅድሜ ዝግጅት መሠረት የተከለከሉ ቁሳቁሶችን እንዳይዙ ጨምረው መክረዋል።

በሽኝቱ ወቅት ጥብቅ ፍተሻ የተደረገ መሆኑን የገለፁት አቶ ኩሴ፤ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ለመፈተን ዝግጁ እንዲሆኑ እና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ በበኩላቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ፈተናውን በድል ለመወጣትና ለአሻጋሪ ውጤት እንዲበቁ መክረዋል፡፡
በመመሪያዎችና ደንቦች መሠረት በተረጋጋ መንፈስ ተፈትነውና ፈተናውን ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ አጠናቀው፣ የላቀ ውጤት በማስመዝግ እንዲሁም ቀድሞ በትምህርት የነበረንን አብላጫ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከወዲሁ መልካም ምኞት እንገልፃለን ብለዋል።

በ2016 በመጀመሪያ ዙር 2 ሸህ 21 የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሽኝት መደረጉን በዞኑ ትምህርት መምሪያ የፈተና ዝግጅት አስተዳደርና የትምህርት ምዘና ጥናት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ኦርካይዶ ጌታ ገልጸዋል።

የሽኝቱ ሙሉ ሂደት ተከታትለን መረጃውን በተከታታይ የሚናደርሳችሁ ይሆናል።







