ወጣቱ ትውልድ ባህሉን በመጠበቅ ዘመናዊ ውዝዋዜን እንዲያውቅ እየሰራ መሆኑን የኮንሶ ዞን ባህልና ቱርዝም መምሪያ አስታወቀ።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን “Ethio-Konso” የተሰኘው ዘመናዊ የክኔት ባንድ አሰልጥኖ አስመረቀ።

በምረቃው ስነ ስርዓት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ህርቶ እንደገለፁት ዘመናዊ የክኔት ባንድ ቡድን እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ከኮንሶ ልዩ ወረዳ መዋቅር ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባህላዊ የክኔት ባንድ ብቻ መኖሩን አስታውሰዋል።

አቶ ገልገሎ አክለውም ዛሬ ላይ ለምረቃ የበቃው “Ethio-Konso” የተሰኘው ዘመናዊ የክኔት ባንድ በልዩ ልዩ የሙዚቃና ውዝዋዜ የሰለጠኑ በመሆናቸው ለአሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበዬሁ በበኩላቸው ዛሬ የተመረቀው “Ethio-Konso” ክኔት ባንድ በ2013 ዓ/ም እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ባንዱ አሁን ባለው ደረጃ በባህላዊ ውዝዋዜዎች እና በኮንሶ ባህላዊ ጭፈራና ውዝዋዜ ብቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዳዊት እንደገለፁት ይህ ተግባር ለወጣት ሠልጣኞች የስራ ዕድል ፈጠራ ሲሆን ዘላቂ የጥበብ ሥራን በንቃት እንዲከውኑ ወጣቱን መክረው፤ ስልጠናውን ለሰጡ አሰልጣኝ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም ከዝግጅት እስከ ምረቃው ድረስ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ሚያዝያ 28/2015 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *