#Ethio_Konso የዘመቻው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በካራት ከተማ አስተዳደር ጃርሶ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተጀምሯል።
በዞናችን በይፋ የተጀመረው የኮቪድ-19ና ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ገዳይ የሆነው የማህፀን በር ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ የበርካታ ህይወትን የነጠቀ፣ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫናዎችን በማሳደሩ ዳግም እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑን የካራት ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሶቴ ዮሐንስ አስረድተዋል።
የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደይጋንቶ ኡርማሌ በዘመቻ ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት ክትባቱ የሰው ልጅ በበሽታ እንዳይጠቃ ከመከላከል ውጪ ሌላ ምስጢር የሌለው በመሆኑ ህብረተሰቡ ከተዛቡ አመለካከቶች በፀዳ መንገድ የሚሰጡ ክትባቶችን በወቅቱ ተከትቦ ከወረርሽኞች ራሱን እንዲከላከል ጥሪ አስተላልፈዋል።
የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ፍሬዘር ኮርባይዶ በበኩላቸው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ከሚሰራባቸው መንገዶች መካከል ክትባት መሆኑን አስገንዝበው ክትባቶቹ በተለያየ ዙር የሚሰጠው በሽታው በተለያየ ጊዜ የሚያገረሽ በመሆኑ ሁሉም ይህንን ተገንዝቦ ክትባቶቹን በሚገባ በመከተብ ጤናውን ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል አሁን እየተሰጠ ያለው የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከመሠረቱ ዕድሜያቸው ከ9-14 ላሉ ልጃገረዶች እንደሚሰጥ ያብራሩት በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የምርምር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ፍሰሐ ለማንጎ ዕድሜያቸው 14 ለሆኑ ልጃገረዶች ብቻ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።
ከኮቪድ-19 በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ7 ሺህ የማህፀን በር ካንሰር ታማሚዎች መካከል ወደ 5ሺህ በላይ በበሽታው እንደሚሞቱና በሽታው እጅግ በጣም አደገኛና ገዳይ በመሆኑ ልጃገረዶችና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ለመከላከያ ክትባቱ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አቶ ፍሰሐ ጨምረው አስገንዝበዋል።
የመከተብ እድል ያገኙ ሁሉ እድለኞች ናቸው! ያሉት የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገልገሎ ገልሾ ድሮ እናቶቻችን ክትባቶች ባለማግኘታቸው ተጎድተዋል ብለዋል።
ተማሪዎች ተከትበው ወደ ማህበረሰቡ በመሄድ ኮሌራን ጨምሮ በአጠቃላይ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ገልገሎ መክረዋል።
ምክትል ዋና አስተዳዳሪው አቶ ገልገሎ ጨምረው ክትባቱ የሚገባቸው እና ታዳጊ ልጃገረዶች እንዲያገኙ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ዘመቻውን በይፋ አስጀምረዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዝያ 25/2015 ዓ/ም







