የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ ለዞኑ ስፖርት ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሲቷ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 12 ዞኖች መካከል በተደረገው የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ በመሳተፋችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ ተናገሩ።
ወጣቱን በሁሉም ስፖርት ዘርፎች በማደራጀትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ወጣቶችን ለሀገር በማብቃትና የስራ ዕድል መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉም ዋና አስተዳደሩ በአቀባበል ወቅት ተናግረዋል።
ሴቶችን በመረብ ኳስ እንዲሁም ወንዶችን በእግር ኳስ በማደራጀትና ጠንካራ ድጋፍ በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለይተን ለውጤታማነት እንሠራለን ብለዋል።
የኮንሶ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና ስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሰለ ጋሼ በበኩላቸው የኮንሶ ዞን ስፖርት ልዑክ በነበረው ስፖርታዊ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኮንሶ ዞን ስፖርት ክለብ በውድድሩ 2 ዋንጫ፣ 9 የወርቅ፣ 11 የብር እንዲሁም 15 የነሐስ በድምሩ 2 ዋንጫና 35 ሜዳሊያዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ማግኘቱን አቶ መሰለ አስረድተዋል።
አቶ መሰለ ጨምረው የኮንሶ ዞን ስፖርት ክለብ በእግር ኳስ፣ በቮሊቦል፣ በባህላዊ ጫወታዎች፣ በቴኳንዶ፣ በቦክስ እንዲሁም በአትሌቲክስ የስፖርት አይነቶች መሳተፋቸውን ገልፀው በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለተደረገላቸው ድጋፍና አቀባበል ልባዊ ምስጋናቸውን ችረዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞንና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዝያ 03/2016 ዓ/ም







