መጋቢት 24 ፍሬዎች ጋር ተያይዞ የተካሄደው ፓናል ውይይት የማጠቃለያ መድረክ

ፓርቲያችን ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ከራስ ጀምሮ እስከ ሀገር በርካታ ለውጦችን ማየት ችለናል፦ ከመጋቢት 24 ፍሬዎች ጋር ተያይዞ በተካሄደው የፓናል ውይይት የማጠቃለያ መድረክ ላይ የተሳተፉ የብልጽግና ሕብረት አባላት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካራት ማዕከል ቢሮዎች ከኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር “ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!” በሚል መሪ-ቃል የመጋቢት 24 ፍሬዎችን አስመልክቶ ያዘጋጁት የፓናል ውይይት መቋጫውን አግኝቷል።

የለውጡ መንግስት ባለፉት ሰባት ዓመታት ባስመዘገባቸው የመጋቢት 24 ድሎችና ፍሬዎች ዙሪያ ሰነድ ያቀረቡት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር-ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ ናቸው።

ሀሳብና አስተያየት ሰጪ የብልጽግና ህብረት አባላት ፓርቲያችን ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ከራስ ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ በርካታ ለውጦችን ማየት ችለናል ያሉ ሲሆን፣ ለውጡን ማስቀጠል የምንችለው ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት በሁሉም አካባቢ ሲኖር ብቻ በመሆኑ ቀጣይ መጋቢት 24ቶችን ደጋግመን እንድንዘክር በሠላም ዕሴት ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ከዚህ ቀደም በዓለም ታሪክ ያልተፃፈና በሀገራችንም ታይቶ የማይታወቅ ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር መካሄዱ እጅግ ትልቅ ኩነት ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ሁሉም አካባቢዎች እንዲለሙ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በመጨረስ፣ እንደ ኮንሶ ዞን ያሉ የመንገድ፣ የውሃ እና የመብራት አቅርቦትና ተደራሽነት ችግሮችን በመቅረፍ፣ እንዲሁም ከዚህ በፊት ቃል ተገብቶ የነበረውን የጎበዝ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ግንባታ ጥያቄን በመመለስ እንደ ዞን ለውጡን ማጽናትና ማስቀጠል አለብን ብለዋል።

በተጨማሪም የለውጦች መመዝገብ ዋና መሠረቱ ተግባብቶ አብሮ መስራት ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ የውስጥና የውጭ ዲፕሎማሲ አድማስን በማስፋት ለሀገራዊ ብልጽግና መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ለለውጡ ማነቆ እየሆኑ ያሉ ብልሹ አሠራሮችን መከላከል ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፤ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን የማጣራትና እርምጃ የመውሰድ ጉዳይም በተመሳሳይ መልኩ ቸል ሊባል የማይገባ ወሳኝ ጉዳይ ነው ሲሉም አሳስበዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው የሀገራችን ኢኮኖሚ በደቀቀበት፣ የፖለቲካ ቀውስ ባጋጠመበት እና ሀገር ትፈርሳለች በተባለበት ማግስት የሰው ልጅ ህይወት ሳይጠፋ በሠላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር በማድረግ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ድል ያገኘንበት የለውጥ ጉዞ ነው ሲሉ ቀኑን አብራርተዋል።

ባሉን ፀጋዎች ላይ ያለንን ጥርጣሬ ያስወገደና በኢኮኖሚው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ያስመዘገብንበት ድንቅ ጉዞ ነው ያሉት ወ/ሮ ወይኒቱ፤ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ደጋግሞ ከማውራት ይልቅ ወደ እድል በመቀየር ለተሻለ ውጤት በትጋት መጣር ያስፈልጋልም ብለዋል ወ/ሮ ወይኒቱ።

ሠላም ከራስ ጀምሮ እስከ ሀገር ይገነባል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ፓርቲያችን ተቋሙን ገንብቶ ሠላምን ለማጽናት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን፤ ሁላችንም ለሠላም ዘብ በመቆም፣ የሠላም አምባሳደር በመሆን እና የወንድማማች/እህትማማችነት ዕሳቤን በማጎልበት አብረን ማደግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ብልጽግና የሚያምነው በተግባር ነው ያሉት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር-ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ በማጠቃለያ ንግግራቸው የተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ተገቢነት ያላቸው በመሆናቸው ወደየሚመለከተው አካል ወስደን በጋራ የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የፓናል ውይይቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተቋጭቷል።

መጋቢት 24/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *