ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን 75 በጎ ፈቃደኛ የተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አባላትን አስመረቀ፣

የኮንሶ ዞን መንገድና ትራንስፖርት ልማት መምሪያ ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን 75 በጎ ፈቃደኛ የተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አባላትን አስመረቀ፣

በካራት ከተማ አስተዳደር ካሉ ሰባት ት/ቤቶች የተውጣጡት እነዚህ የተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ዛሬ ለምረቃ በቅተዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሊታ ተመራቂዎቹ በጎ ፍቃደኛ የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች በትምህርት ቤት መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ ትራፊኮችን በማገዝ፣ እንደዚሁም ለተማሪዎችና ለአከባቢው ህብረተሰብ ስለ መንገድ ደህንነት በማስተማር የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወጡ አስረድተዋል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ኢ/ር ጌታቸው ጉዴታ በበኩላቸው ተመራቂዎቹ በመንገድ ደህንነት ላይ ተጨማሪ አጋዥ ኃይል መሆናቸውን በመጠቆም በት/ት ቤታቸውና በከተማችን ያለውን የመንገድ ደህንነትን የማስጠበቅ ስራ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ተመራቂዎቹ በሥልጠና ወቅት ያገኙትን የሃሳብና የተግባር ልምምድ በካራት ከተማ አደባባይ በትርዒት መልክ አሳይተዋል።

የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት ልማት መምሪያ፣ እንደዚሁም የካራት ከተማ አስተዳደር እና የካ/ዙሪያ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ዩኒት ለ45 የተማሪ ትራፊኮች ሙሉ ልብስ ያበረከቱ ሲሆን፣ በስልጠናው ወቅት ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እና ለተመራቂዎቹ የዕውቅና ሰርትፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

በምርቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የዞኑን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሊታን ጨምሮ፣ የዞኑ ህዝብ ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገረመው አያኖ፣ የዞኑ ህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ገረሙ ካይሲሞ፣ የዞኑ ትራፊክ ፖሊስ አባላት፣ ተመራቂ የተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አባላት እንዲሁም መምህራን እና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

መጋቢት 04/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *