በኮንሶ ዞን የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በይፋ ተጀመረ

ካራት፣ መስከረም 5/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) ፣፟ በኮንሶ ዞን የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዞንና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የትምህርት ባለሙያዎችና የትምህርት ቤት አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል። በዞኑ በሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ነባርና አዳዲስ ተማሪዎችን በመቀበልና የመማር ማስተማር ሥራን በማስጀመር የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀምሯል።

ተማሪዎች ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በሥነ ልቦና ለመማር ዝግጁ መሆን፣ ሰዓትን ማክበርና በትምህርት ሰዓታቸው በወቅቱ መገኘት እንዳለባቸውም በመምከር ፣ራሳቸውንና መምህራኖቻቸውን ማክበር፣ መቅረትና ማርፈድን ልማድ አለማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው፣ መቅረትና ማርፈድ ከትምህርት ውጤት መቀነስ ዋና መንስኤዎች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል። ተማሪዎች ሁልጊዜ አዳዲስ እውቀቶችን ለመቅሰም ዝግጁ በመሆን፣ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በትጋት እንዲማሩና ራሳቸውን ለቀጣይ ኃላፊነት እንዲያዘጋጁም አሳስበዋል።

የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አሸናፊ በርሻ በበኩላቸው፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 5 መጀመሩን ገልጸው ፣ በዞኑ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም የትምህርት ዘመኑን በወቅቱ ለማስጀመር ነባርና አዳዲስ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሥራቸውን ማስጀመራቸውን አስታውቀዋል። ተማሪዎችም የትምህርት ሥርዓቱ በወቅቱ እንዲጀመርና የመማር ማስተማር ሥራው በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሠረት እንዲከናወን ተገቢውን ዝግጅት አድርገው ወደ ትምህርት ቤቶቻቸው እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በካራት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና የመንግሥት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጉራሾ ለሚታ በበኩላቸው፣ ትውልድ በመምህር ይቀርጻል ሃገር በትምህርት ትበለጽጋለች ብለው፣ የትምህርት ዘመኑን በወቅቱ መጀመር በትምህርት ውጤት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገልጸዋል። አቶ ጉራሾ ለሚታ ከመርሃ ግብሩ ተሳታፊ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን በትምህርት ቤቱ እየተገነባ የሚገኘውን ሕንፃ ጎብኝተው ፣ ሕንፃው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠናቅቆ ለተማሪዎች አገልግሎት መዋል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻሁን ኩሲያ በበኩላቸው፣ በጊዜ መገኘትና እውቀትን መቅሰም ለተሻለ ውጤት የሚያደርሱ መሠረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸው፣ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በትጋት መማርና መምህራንን ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል። ተማሪዎች የሀገር ተረካቢ ትውልድ በመሆናቸው፣ በትምህርት ዘመኑ በትጋት መማርና ራሳቸውን ለተሻለ ኃላፊነት ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *